የአባቶች አለቃ፣ ፓትሪያርክ ደግሞም ሟች አባት; ወንጌል ሰባኪ; የመልከ ጼዴቅ ክህነት; የፓትሪያርክ በረከቶች ተመልከቱ ቅዱሣት መጻህፍት ለዚህ ሁለት አይነት ትርጉም ይሰጣሉ፥ (፩) በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ የተሾመ ሀላፊነት፣ አንዳንዴም ወንጌል ሰባኪ ተብለው ይጠራሉ፤ (፪) የቤተሰቦች አባቶች። የተሾሙ ፓትሪያርኮች ብቁ ለሆኑ የቤተክርስቲያን አባላት ልዩ በረከቶችን ይሰጣሉ። የተሾሙ ፓትሪያርክ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች ሰጠ, ኤፌ. ፬፥፲፩ (እ.አ. ፩፥፮). ወንጌል ሰባኪዎችን መሾም የአስራሁለቱ ሀላፊነት ነው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፴፱. ሀይረም ክህነት እና የፓትሪያርክ ሀላፊነትን ይውሰድ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፺፩–፺፪፣ ፻፳፬፤ ፻፴፭፥፩. አባቶች ያዕቆብ ልጆቹን እና ትውልዶቻቸውን ባረከ, ዘፍጥ. ፵፱፥፩–፳፰. ስለ አባቶች አለቃ ዳዊት በግልጥ ልናገር, የሐዋ. ፪፥፳፱. ሌሂ ትውልዶቹን መከረ እናም ባረከ, ፪ ኔፊ ፬፥፫–፲፩. መብት ያለው ወራሽ፣ የአባቶችን መብት የሚይዘው ሊቀ ካህን ሆንኩኝ, አብር. ፩፥፪–፬.