የጥናት እርዳታዎች
አብርሐም


አብርሐም

ከለዳውያን ዑር ውስጥ የተወለደ፣ የታራን ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፲፩፥፳፮፣ ፴፩፲፯፥፭)። የምድር ህዝቦች ሁሉ የሚባረኩበት ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ጌታ የገባለት የጌታ ነቢይ። አብርሐም በመጀመሪያ አብራም ተብሎ ይጠራ ነበር።

መፅሐፈ አብርሐም

በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) ወደ ቤተክርስቲያኗ እጅ የገባ በአብርሐም የተጻፈ የጥንት መዝገቦች። መዝገቦቹ እና አንዳንድ አስከሬኖች በግብፅ መቃብሮች ውስጥ በአንቶኒዮ ሌቦሎ ተገኝተው ነበር፣ እነዚህንም ለማይክል ቻንድለር በኑዛዜ ቃል ተወለት። በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) ቻንድለር እነዚህን በዩናትድ ስቴት ውስጥ ለእይታ አቀረባቸው። አንዳንድ የጆሴፍ ስሚዝ ጓደኞች ገዙአቸው እና ለነብዩ ሰጡት፣ እርሱም ተረጎማቸው። ከእነዚህ አንዳንድ ፅሁፎችም በየታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ ይገኛሉ።

ምዕራፍ ፩ አብርሐም ክፉ ቄሶች ሊሰዉት በሞከሩበት በከላውዴዎ ዑር ውስጥ ስለነበረው አጋጣሚዎች ይመዘግባል ምዕራፍ ፪ ስለከነዓን ጉዞው ይናገራል። ጌታም ታየው እና ቃል ኪዳን ከእርሱም ጋር ገባ። ምዕራፍ ፫ አብርሐም ሁለንተናን እንዳየ እና በሰማያዊ ሰውነቶች መካከል ያለውን ግንኙነቶች እንደተመለከተ መዝግቧል። ምዕራፍ ፬–፭ የፍጥረት ሌላ መዝገቦች ናቸው።

የአብርሐም ዘር

ለህግጋት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ስነስርዓቶች ታዛዥ በመሆን እግዚአብሔር ለአብርሐም የገባውን የተስፋ ቃላትና ቃል ኪዳኖች የሚቀበሉ ህዝቦች። ወንዶች እና ሴቶች የእውነት የአብርሐም ዝርያ ከሆኑ ወይም ወንጌልን በመቀበል እና በመጠመቅ ወደ ቤተሰቡ በጉዲፈቻ ከተወሰዱ እነዚህን በረከቶች ይቀበላሉ (ገላ. ፫፥፳፮–፳፱፬፥፩–፯ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፫–፴፬፻፫፥፲፯፻፴፪፥፴–፴፪አብር. ፪፥፱–፲፩)። ለአብርሐም የእውነት ዘሮች በረከቶቻቸውን ታዛዥ ባለመሆን ለማጣት ይችላሉ (ሮሜ ፬፥፲፫፱፥፮–፰)።