ሊያሆና በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ሁለት መጠቆሚያዎች የነበረው እናም ደግሞም እንደ አቅጣጫ መለያ መሳሪያ ለሌሂና ጻድቅ ለሆኑት ተከታዮቹ መንፈሳዊ መመሪያ የሚሰጥ የነሀስ ኳስ። ጌታ ሊያሆናውን ሰጠ እናም በዚህ በኩል መመሪያዎችን ሰጠ። ሌሂ ሁለት እንዝርቶች የነበሩት ሌሂ እና ቤተሰቡ መሄድ ያለባቸውን አቅጣጫ የሚጠቁም በነሐስ የተሰራ ክብ ኳስ አገኘ, ፩ ኔፊ ፲፮፥፲. ኳሱ የሚሰራው ለእነርሱ በሚሰጣቸው እምነትና ትጋት መሰረት ነው, ፩ ኔፊ ፲፮፥፳፰–፳፱ (አልማ ፴፯፥፵). ቢንያም ኳሱን ለሞዛያ ሰጠ, ሞዛያ ፩፥፲፮. ኳስ ወይንም ጠቋሚ ሊያሆና ይባላል, አልማ ፴፯፥፴፰. ሊያሆና ከክርስቶስ ቃል ጋር ተነጻጽሯል, አልማ ፴፯፥፵፫–፵፭. የመፅሐፈ ሞርሞን ሶስት ምስክሮችለሌሂ የተሰጠውን ጠቋሚ ይመለከታሉ, ት. እና ቃ. ፲፯፥፩.