ክብር ደግሞም መቆጠር; ማክበር; ብርሀን፣ የክርስቶስ ብርሀን; እውነት; የክብር ደረጃዎች ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ክብር ስለእግዚአብሔር ብርሀንና እውነት የሚያመለክት፣ ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ነገር አምልኮን ማሳየት ነው። ይህም ደግሞ ስለ ሙገሳ ወይም ክብር እናም ስለዘለአለማዊ ህይወት አንዳንድ ጉዳዮች ወይም ስለእግዚአብሔር ክብር ያመለክታል። አባትህንና እናትህን አክብር, ዘፀአ. ፳፥፲፪ (፩ ኔፊ ፲፯፥፶፭; ሞዛያ ፲፫፥፳). እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር, ምሳ. ፫፥፱. ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች, ኢሳ. ፮፥፫ (፪ ኔፊ ፲፮፥፫). የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል, ዮሐ. ፲፪፥፳፮. እኛም ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን, ፪ ቆሮ. ፫፥፲፰. ባሎች ለሚስቶቻቸው ክብር ይስጧቸው, ፩ ጴጥ. ፫፥፯. በከንፈሮቻቸውም ጌታን አከበሩ, ፪ ኔፊ ፳፯፥፳፭ (ኢሳ. ፳፱፥፲፫). በክብር ከእርሱ ጋር እንድኖር በመጨረሻው ቀን ያስነሳኛል, አልማ ፴፮፥፳፰. የዓለምን ክብር አይደለም የምፈልገው, አልማ ፷፥፴፮. ኃይሌ የሆነውን ክብርህን ስጠኝ በማለት ዲያብሎስ በእኔ ላይ አመጸ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፮. ታማኝ በክብር ዘውድ አክሊልም ይጫንላችኋል, ት. እና ቃ. ፸፭፥፭ (ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፶፭). ጌታ የሚያገለግሉትንም ለማክበር ይደሰታል, ት. እና ቃ. ፸፮፥፭. በትንሳኤ የምንቀበለው ክብር በጽድቅ መሰረት ይለያያል, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፻፲፱. ፴፮ የእግዚአብሔር ክብር የመረዳት ችሎታ ነው, ት. እና ቃ. ፺፫፥፴፮. ያልተመረጡት በሰዎች ለመከበር ስለሚነሳሱ ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፬–፴፭. የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት አምጥቶም ማሳለፍ የእግዚአብሔር ስራ እና ክብር ነው, ሙሴ ፩፥፴፱. ብርሀናቸውና ክብራቸው የሚገለጽበት ሁሉ ብቁ ያልሆነ፣ ሁለት ሰዎች በአየር ከእኔ በላይ ቆመው አየሁ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፯. ህግን በማክበርና በመደገፍ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፪ (ት. እና ቃ. ፻፴፬፥፮).