የጥናት እርዳታዎች
ጋድ፣ የያዕቆብ ልጅ


ጋድ፣ የያዕቆብ ልጅ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የያዕቆብና የዘለፋ ልጅ (ዘፍጥ. ፴፥፲–፲፩)። ትውልዶቹ የእስራኤል ጎሳ ሆኑ።

የጋድ ጎሳ

ያዕቆብ ለልጁ ጋድ የሰጠውን በረከት ለማየት ኦሪት ዘፍጥረት ፵፱፥፲፱ ተመልከቱ። ሙሴ ለጋድ ጎሳ ለሰጠው በረከት ኦሪት ዘዳግም ፴፫፥፳–፳፩ ተመልከቱ በእነዚህ በረከቶች መሰረት፣ የጋድ ትውልዶች ጦርነት የሚወዱ ዘሮች ነበሩ። በከነዓን ምድር ውስጥ የተመደበላቸው መሬት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ በኩል ነበር እናም ጥሩ የግጦሽ መሬት እና በቂ ውሀ ያለበት ነበር።