መገሰጽ፣ ተግሳጽ ደግሞም ጭንቀት ተመልከቱ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን ለማሻሻል ወይም ለማጠናከር ለመርዳት የሚሰጥ ማስተካከያ ወይም ቅጣት። ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ, ኢዮብ ፭፥፲፯ (ምሳ. ፫፥፲፩). አቤቱ… አንተ የገሠጽኸው … ሰው ምስጉን ነው, መዝ. ፺፬፥፲፪. ሁሉም ቅዱሣት መጻህፍት ለትምህርትና ለተግሣጽ የተሰጠ ነው, ፪ ጢሞ. ፫፥፲፮. ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋል, ዕብ. ፲፪፥፭–፲፩. ጌታ ህዝቡን መግሰፅ ተገቢ መሆኑን አየ, ሞዛያ ፳፫፥፳፩–፳፪. ጌታ ህዝቡን ካልገሰጸ፣ አያስታውሱትም, ሔለ. ፲፪፥፫. ጌታ የያሬድ ወንድምን አነጋገረው፣ እናም ገሰፀው, ኤተር ፪፥፲፬. ንስሀ ይገቡ ዘንድ ተገሰጹ, ት. እና ቃ. ፩፥፳፯. የምወዳቸውንም ኀጥያታቸውን ለመሰረይ እገስጻቸዋለሁ, ት. እና ቃ. ፺፭፥፩. በግሰጻው የማይጸኑት ሁሉ ሊቀደሱ አይችሉም, ት. እና ቃ. ፻፩፥፪–፭. ህዝቦቼ ታዛዥነትን እስከሚማሩ ድረስ መገሰጽ ያስፈልጋቸዋል, ት. እና ቃ. ፻፭፥፮. መገሰፅን ለመቀበል የማይችል ለመንግስቴ ብቁ አይደለም, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፩.