የወይራ ዛፍ ደግሞም እስራኤል; ዘይት ተመልከቱ በእስራኤል ውስጥ በልምድ የሚገኝ እና በመፅሐፍ ቅዱስ ምድሮች ውስጥ አስፈላጊ የእርሻ ጥሬ እቃ የሆነ ዛፍ። የሚያድገውም ለእንጨቱ፣ ለፍሬው፣ እና ለዘይቱ ነበር። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደ እስራኤል ቤት ምሳሌ የወይራ ዛፍን በብዛት ይጠቀሙበት ነበር። የእስራኤልን ቤት ልክ ቅርንጫፎቹ እንደወደቁበትና እንደተበተኑት ወይራ ዛፍ ተነፃፀረዋል, ፩ ኔፊ ፲፥፲፪ (፩ ኔፊ ፲፭፥፲፪). ጌታ የእስራኤል ቤትን ከወይራ ዛፍ ጋር አነጻጸረ, ያዕቆ. ፭–፮. ጌታ የክፍል ፹፰ ራዕይን የወይራ ዛፍ ቀጠል ብሎ ጠራ, ት. እና ቃ. ፹፰ ማስተዋወቂያ. ልዑል ሰው አገልጋዮቹን ወደ ወይን አትክልት ስፍራው እንዲሄዱ እና አስራ ሁለት የወይራ ዛፎች እንዲተክሉ ነገራቸው, ት. እና ቃ. ፻፩፥፵፫–፷፪.