የጥናት እርዳታዎች
ምሳሌዎች


ምሳሌዎች

አንድ ነገርን እንደ ሌላ ነገር ተመሳሳይነት ወይም ምስል መጠቀም። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ ምሳሌዎችን የተለመዱ እቃዎችን፣ ድርጊቶችን፣ ወይም ጉዳዮችን የወንጌል መሰረታዊ መርሆችን ወይም ትምህርቶችን ለመወከል ይጠቀሙባቸዋል። ለምሳሌ፣ የመፅሐፎፈ ሞርሞን ነቢይ አልማ የእግዚአብሔር ቃልን ለመወከል ዘርን ተጠቅሞበታል (አልማ ፴፪)።

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ በሙሉ ነቢያት ምሳሌዎችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ለማስተማር ተጠቅመዋል። የተጠቀሙባቸው አንዳንዶቹ ምሳሌዎች በተጨማሪም ስርዓቶች (ሙሴ ፮፥፷፫)፣ መስዋዕቶች (ዕብ. ፱፥፲፩–፲፭ሙሴ ፭፥፯–፰)፣ ቅዱስ ቁርባን (ጆ.ስ.ት.፣ ማር. ፲፬፥፳–፳፬ሉቃ. ፳፪፥፲፫–፳)፣ እና ጥምቀት። (ሮሜ ፮፥፩–፮ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፲፪–፲፫) ነበሩ። ብዙዎቹ የመፅሐፍ ቅዱስ ስሞች ምሳሌዎች ነበሩ። በብሉይ ኪዳን ውስጥ የድንኳን ስነስርዓቶች እና የሙሴ ህግ የዘለአለም እውነቶችን ይወክላሉ(ዕብ. ፰–፲ሞዛያ ፲፫፥፳፱–፴፪አልማ ፳፭፥፲፭ሔለ. ፰፥፲፬–፲፭)። ለሌሎች ምሳሌዎች ማቴዎስ ፭፥፲፫–፲፮ዮሐ. ፫፥፲፬–፲፭ያዕቆ. ፬፥፭አልማ ፴፯፥፴፰–፵፭ ተመልከቱ።