ያሬዳውያን ደግሞም መፅሐፈ ሞርሞን; የያሬድ ወንድም; ያሬድ ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የያሬድ፣ የወንድሙ፣ እና የጓደኞቻቸው ትውልዶች የሆኑ ህዝቦች (ኤተር ፩፥፴፫–፵፩)። በእግዚአብሔር ከባቢሎን ማማ ወደ ቃል ኪዳን ምድር ወደ አሜሪካዎች ተመርተው ነበር (ኤተር ፩፥፵፪–፵፫፤ ፪–፫፤ ፮፥፩–፲፰)። በአንድ ጊዜ ብዙ ሚልዮን ህዝቦች የነበራት ሀገር ቢኖራቸውም፣ በኃጢያት ምክንያት በመጣ ጦርነት ምክንያት ተደምስሰው ነበር (ኤተር ፲፬–፲፭)።