ኩነኔ ደግሞም መንፈሳዊ ሞት; ሲዖል; የጥፋት ልጆች; ዲያብሎስ ተመልከቱ ከማደግ መወገድና በእግዚአብሔርና በክብሩ ፊት ለመቅረብ መወገድ። ፍርድ (ኩነኔ) የሚገኘው በተለያዩ ደረጃዎች ነው። ሙሉ የሰለስቲያል ዘለአለማዊነትን የማያገኙት በሙሉ በእድገታቸው እና በመብቶቻቸው በትንሽም ደረጃ ይወገዳሉ፣ እና በዚህም መጠን የተፈረደባቸው (የኮነኑ) ናቸው። እናንተ ግብዞች ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ, ማቴ. ፳፫፥፲፬. በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል, ማር. ፫፥፳፱. ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ, ዮሐ. ፭፥፳፱ (፫ ኔፊ ፳፮፥፭). ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና, ፩ ቆሮ. ፲፩፥፳፱ (፫ ኔፊ ፲፰፥፳፰–፳፱). ንስሀ የማይገቡ፣ እናም የማይጠመቁ፣ እና እስከመጨረሻው የማይጸኑ መኮነን ይገባቸዋል, ፪ ኔፊ ፱፥፳፬ (ማር. ፲፮፥፲፮; ኤተር ፬፥፲፰; ት. እና ቃ. ፷፰፥፱; ፹፬፥፸፬). ክፉዎች ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ከተኮነኑት ነፍሳት ጋር በሲዖል ከመኖር በላይ አሰቃቂ ነው, ሞር. ፱፥፬. እስከሚታዘዝ ድረስ ምንም የማያደርገው፣ እርሱም የተኮነነ ነው, ት. እና ቃ. ፶፰፥፳፱. አዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳንን ሙላት የሚቀበልም በህጉ ይኑር፣ ወይም ይኮነናል, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፮.