ኦሪት ዘሌዋውያን
በእስራኤል ውስጥ ስላሉት የካህናት ሀላፊነቶች የሚነግር የብሉይ ኪዳን መፅሐፍ። የእግዚአብሔርን ቅዱስነት እናም ህዝቦቹ ቅዱስ ለመሆን በሚችሉበት ህግ ላይ ያተኩራል። አላማውም የሙሴን ህግ የስነምግባር አስተያየት እና ሀይማኖታዊ እውነቶችን በቅድመ ተከተል ለማስተማር ነው። ሙሴ ኦሪት ዘሌዋውያንን ጽፏል።
ምዕራፍ ፩–፯ የመስዋዕት ስነስርዓቶችን ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፰–፲ ካህናትን ለመቀደስ የሚደረጉትን ቅድመ ተከተል ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፲፩ ምን መበላት እንደሚቻልና እንደማይበላ እናም ምን ንጹህ እንደሆነና እንዳልሆነ ይገልጻል። ምዕራፍ ፲፪ ሴቶች ልጆች ከወለዱ በኋላ ስለሚያደርጉት ይወያያል። ምዕራፍ ፲፫–፲፭ ከርኩስነት ስነስርዓቶች ጋር ስለሚገናኙ ህግጋት ይናገራሉ። ምዕራፍ ፲፮ በማስተስረያ ቀን ስለሚከናወኑት ቅድመ ተከተል ያይዘ ነው። ምዕራፍ ፲፯–፳፮ ስለሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ ስነስርዓት ጋር የተገናኙ የህግጋት ደንቦችን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፳፯ እስራኤልን ምርታቸውን፣ መንጋዎቻቸውን፣ እና ከብቶቻቸውን ለጌታ እንዲቀድሱ ጌታ ያዘዛቸውን ይገልጻል።