ሙዚቃ ደግሞም መዘመር; መዝሙር ተመልከቱ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጊዜዎች ጀምሮ ደስታን፣ ሙገሳን፣ እና ማምለክን ለመግለጽ የሚጫወቱት ቃናዎች እና የሙዚቃ ምቶች (፪ ሳሙ. ፮፥፭)። ይህም የጸሎት አይነት ለመሆን ይችላል። መዝሙረ ዳዊት በቀላል ቃናዎች እና በመሳሪያዎች እጀባ የተዘመሩ ነበሩ። የአሮን እና የሙሴ እኅት ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ እናም እርሷና ሴቶችም ጨፈሩ, ዘፀአ. ፲፭፥፳. መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም እየመቱ ነበር፣ ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር, ፪ ዜና ፭፥፲፪. ኢየሱስና ሐዋሪያት ከመጨረሻው እራት በኋላ መዝሙርም ዘመሩ, ማቴ. ፳፮፥፴. በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ አስተምሩ, ቄላ. ፫፥፲፮. የቤዛነት የፍቅር ዜማ ለመዘመር ተሰምቷችኋል, አልማ ፭፥፳፮. የጌታ ነፍስ በልብ መዝሙር ትደሰታለች፣ አዎ የጻድቅን መዝሙር ለእኔ ጸሎት ነው, ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፪. ጌታን በዘፈን፣ በሙዚቃ፣ እና በእስክስታ አምልኩ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፰.