የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ደግሞም መወለድ; ሰው፣ ሰዎች; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; የክርስቶስ ልጆች; ዳግመኛ መወለድን፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ተመልከቱ ቅዱሣት መጻህፍት እነዚህን አባባሎች በሁለት መንገድ ተጠቅመውባቸዋል። በአንድ አስተያየት፣ ሁላችንም የሰማይ አባታችን የመንፈስ ልጆች ነን። በሌላ አስተያየት፣ የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል እንደገና የተወለዱት ናቸው። የአብ የመንፈስ ልጆች አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ, መዝ. ፹፪፥፮. የእግዚአብሔር ዘመዶች ነን, የሐዋ. ፲፯፥፳፱. ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛ ይገባናል, ዕብ. ፲፪፥፱. የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ, ሙሴ ፩፥፲፫. በኃጢያት ክፍያ በኩል እንደገና የተወለዱ ልጆች ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው, ዮሐ. ፩፥፲፪ (ሮሜ ፰፥፲፬; ፫ ኔፊ ፱፥፲፯; ት. እና ቃ. ፲፩፥፴). አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን, ፩ ዮሐ. ፫፥፩–፪. የክርስቶስ ልጆች፣ ወንዶች እና ሴት ልጆቹ፣ ተብላችሁ ትጠራላችሁ, ሞዛያ ፭፥፯. ሁሉም ሰው፣ ወንዶችና ሴቶች፣ በድጋሚ መወለድ ይገባቸዋል, ሞዛያ ፳፯፥፳፭. እነርሱም ወንድና ሴት ልጆቼም ይሆናሉ, ኤተር ፫፥፲፬. በእርግጥ እናንተ የክርስቶስ ልጆች ትሆናላችሁ, ሞሮኒ ፯፥፲፱. ወንጌሌን የሚቀበሉ ሁሉ በመንግስቴ ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች ናቸው, ት. እና ቃ. ፳፭፥፩. እነርሱ አማልክቶች፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶፰. እንደዚህ ሁሉም የእኔ ልጆች መሆን ይችላሉ, ሙሴ ፮፥፷፰. ብዙዎችም አመኑና የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ, ሙሴ ፯፥፩.