የጥናት እርዳታዎች
ምኩራብ


ምኩራብ

ለሀይማኖት አላማዎች የሚጠቀሙባቸው የመሰብሰቢያ ቦታዎች። በአዲስ ኪዳን ጊዜዎች፣ የምኩራብ እቃዎች የህግ እና ሌሎች ቅዱስ ጽሁፎች የነበረባቸውን ጥቅልል የያዘ ታቦት፣ የማንበቢያ ጠረጴዛ፣ እና የሚያመልኩት የሚቀመጡበት ያለው ብቻ ነበር።

የአካባቢው የሽማግሌዎች ሸንጎ እያንዳንዱን ምኩራብ ያስተዳድራሉ። እነርሱ ማን መግባት እንደሚችል እና ማን መግባት እንደማይችል ይወስናሉ (ዮሐ. ፱፥፳፪፲፪፥፵፪)። በጣም አስፈላጊ የሆነው ባለስልጣን የምኩራቡ አስተዳዳሪ ነው (ማር. ፭፥፳፪ሉቃ. ፲፫፥፲፬)። እርሱም በአጠቃላይ ጸሀፊ፣ ህንጻውን የሚጠብቅ፣ እና አገልግሎትን የሚያስተዳድር ነበር። አጃቢዎችም የጸሀፊ ሀላፊነቶችን ይፈጽማሉ (ሉቃ. ፬፥፳)።

አይሁዶች በሚኖሩበት፣ በፍልስጥኤም ይሁን በሌላ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ምኩራቦች ይገኙ ነበር። ይህም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማሰራጨት ታላቅ እርዳታ ነበር ምክንያቱም የቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ሚስዮናውያን በምኩራብ ውስጥ ለመናገር ይችሉ ነበር (የሐዋ. ፲፫፥፭፣ ፲፬፲፬፥፩፲፯፥፩፣ ፲፲፰፥፬)። እንደዚህ አይነት ነገሮች በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ይገኙ ነበር (አልማ ፲፮፥፲፫፳፩፥፬–፭፴፪፥፩) በዚህ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ሚስዮናውያንም እንደዚህ ይደረግ ነበር (ት. እና ቃ. ፷፮፥፯፷፰፥፩)።