አሶር
በብሉይ ኪዳን ዘመናት ውስጥ በሙሉ፣ ከተወዳዳሪዋ ባብሎን ጋር፣ ሶርያን እና ፍልስጥኤምን የገዛች የጥንት ግዛት። ምንም እንኳን አሶራውያን ከ፲፪ኛው ሺህ ም.ዓ. ግማሽ እስከ ፯ኛው ሺህ ም.ዓ. መጨረሻ ድረስ ታላቅ ሀይል የነበሩ ቢሆኑም፣ የረጋ የፖለቲካ ድርጅት ለመገንባት በምንም አልቻሉም ነበር። በፍርሀት፣ ጠላቶቻቸውን በእሳት እና በጎራዴ በመደምሰስ ወይም የጠላቶቻቸውን ህዝቦች ታላቅ ክፍልን ወደ ግዛቶቻቸው ሌላ ክፍሎች በመላክ ደካማ እንዲሆኑ በማድረግ ይገዙ ነበር። በአሶራውያን ተገዢነት ስር የነበሩት ህዝቦች ከመንግስት ጋር ሁልጊዜም ይታገሉ ነበር። (፪ ነገሥ. ፲፰–፲፱፤ ፪ ዜና ፴፪፤ ኢሳ. ፯፥፲፯–፳፤ ፲፤ ፲፱፤ ፴፯ ተመልከቱ።)