ወደ ዕብራውያን መልእክት
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያለ መፅሐፍ። ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ የጻፈው አይሁድ የሆኑትን የቤተክርስቲያን አባላት አብዛኛዎቹ የሙሴ ህግ በክርስቶስ እንደተሟላ እና የክርስቶስ ታላቁ የወንጌል ህግ ይህን እንደተካ ለማሳመን ነበር። ከሶስተኛው ሚስዮኑ መጨረሻ ላይ (በ፷ ም.ዓ. አካባቢ) ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ፣ ብዙዎቹ የቤተክርስቲያኗ አይሁድ አባሎች የሙሴን ህግ እያከበሩ እንዳሉ አገኛቸው (የሐዋ. ፳፩፥፳)። ይህም በኢየሩሳሌም የነበረው የቤተክርስቲያኗ ጉባኤ አንዳንድ የሙሴ ህግ ስነስርዓቶች ለአህዛብ ክርስቲያኖች አስፈላጊ እንዳልሆነ ከተወሰነ ከአስር አመት በኋላ ነበር። ጳውሎስ ከዚህ በኋላ በእራሳቸው ቅዱሣት መጻህፍት እና ግልፅ ምክንያት በመስጠት የሙሴን ህግ ከዚህ በኋላ ለምን መከተል እንደማያስፈልጋቸው ወደ ዕብራውያን እንደጻፈ ግልፅ ነው።
ምዕራፍ ፩ እና ፪ ኢየሱስ ከመላእክት በላይ ታላቅ እንደሆነ ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፫–፯ ኢየሱስን ከሙሴና ከሙሴ ህግ ጋር ያነጻጽራሉ እናም እርሱ ከሁለቱም ታላቅ እንደሆነ ይመሰክራሉ። የመልከ ጼዴቅ ክህነት ከአሮናዊ ክህነት ታላቅ እንደሆነም ያስተምራሉ። ምዕራፍ ፰–፱ የሙሴአዊ ስነስርዓቶች ሰዎችን ለክርስቶስ አገልግሎት እንዴት እንደሚያዘጋጁና ክርስቶስ እንዴት የአዲሱ ቃል ኪዳን አማላጅ እንደሆነ ይገልጻሉ (አልማ ፴፯፥፴፰–፵፭፤ ት. እና ቃ. ፹፬፥፳፩–፳፬)። ምዕራፍ ፲ ለትጉነትና ታማኝነት የሚገፋፋ ነው። ምዕራፍ ፲፩ የእምነት ፅሁፍ ነው። ምዕራፍ ፲፪ ግሰጻን እና ሰላምታን ይሰጣል። ምዕራፍ ፲፫ ስለጋብቻ ክብር እን ስለታዛዥነት አስፈላጊነት ይናገራል።