ሀሳቦች ደግሞም ማሰላሰል; ነጻ ምርጫ ተመልከቱ በሰው አዕምሮ ውስጥ የሚገኝ አስተያየት፣ ግንዛቤ፣ እና ቅርፅ የማሰብ ሀይል የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፣ እናም የማሰብ ሀይላችንን እንዴት እንደምንጠቀምባቸው ለመምረጥ ነጻ ነን። አስተሳሰባችን አስተያየታችን እና ጸባያችን ላይ፣ እንዲሁም ከዚህ ህይወት በኋላ በሚኖረን ህይወት ላይ ተፅዕኖ አለው። ጻድቅ ሀሳቦች ወደ ደህንነት ይመራሉ፣ ክፉ ሀሳቦች ወደ መኮነን ይመራሉ። እግዚአብሔር የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃል, ፩ ዜና ፳፰፥፱. በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነው, ምሳ. ፳፫፥፯. አሳቤ እንደ አሳባችሁ አይደሉም, ኢሳ. ፶፭፥፯–፱. ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አወቀ, ማቴ. ፲፪፥፳፭ (ሉቃ. ፭፥፳፪; ፮፥፰). ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ ይመጣል, ማር. ፯፥፳–፳፫. ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን, ፪ ቆሮ. ፲፥፭. መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ, ፊልጵ. ፬፥፰. ስለዓለም ማሰብ ሞት እንደሆነና፣ ስለመንፈሳዊ ነገር ማሰብ ዘለዓለማዊ ህይወት እንደሆነ አስታውሱ, ፪ ኔፊ ፱፥፴፱. ራሳችሁን፣ እናም ሀሳባችሁን፣ የማታስተውሉ ከሆናችሁ፣ መጥፋት ይገባችኋል, ሞዛያ ፬፥፴. ሀሳባችንም ደግሞ ይፈርድብናል, አልማ ፲፪፥፲፬. ከእግዚአብሔር ብቻ የሃሳብህንና የልብህን ፈቃድ ያውቃል, ት. እና ቃ. ፮፥፲፮ (ት. እና ቃ. ፴፫፥፩). በማንኛውም ሃሳብ ወደእኔ ተመልከቱ, ት. እና ቃ. ፮፥፴፮. የህይወትን ቃል በአዕምሮዎቻችሁ ውስጥ አከማቹ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፹፭. ጥቅም የሌላቸውን ሀሳቦቻችሁን ጣሉ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፱. የሰዎችን የልባቸውን ሀሳቦቻቸውን ይገልጻል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፱. ምግባረ ጥሩነትም ሀሳብህን ያሳምር, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፭. የእያንዳንድ ሰው አሳብ ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ ሆነ, ሙሴ ፰፥፳፪.