መሀሪ፣ ምህረት ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ይቅርታ ማድረግ; ጸጋ; ፍትህ ተመልከቱ የርህራሄ፣ የደግነት፣ እና የምህረት መንፈስ። ምህረት ከእግዚአብሔር ጸባያት አንዱ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢያት በሚከፍለው መስዋዕቱ በኩል ምህረትን ያቀርብልናል። እግዚአብሔር መሐሪና ባለ ብዙ ቸርነት ነው, ዘፀአ. ፴፬፥፮ (ዘዳግ. ፬፥፴፩). ምህረቱም ለዘላለም ነው, ፩ ዜና ፲፮፥፴፬. ቸርነትህና ምሕረትህ ይከተሉኛል, መዝ. ፳፫፥፮. ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉ ነው, ምሳ. ፲፬፥፳፩. ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወድዳለሁ, ሆሴ. ፮፥፮. የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና, ማቴ. ፭፥፯ (፫ ኔፊ ፲፪፥፯). እናንተ ግብዞች አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ, ማቴ. ፳፫፥፳፫. አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ, ሉቃ. ፮፥፴፮. እንደ ምሕረቱ መጠን አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም, ቲቶ ፫፥፭. የጌታ ምህረቶች ርህራሄ በሁሉም ላይ ናቸው, ፩ ኔፊ ፩፥፳. ምህረት ንስሀ በማይገባው ሰው ላይ ምንም ሥፍራ አይኖራትም, ሞዛያ ፪፥፴፰–፴፱. እግዚአብሔር በስሙ ለሚያምኑት ሁሉ መሃሪ ነው, አልማ ፴፪፥፳፪. ምህረት የፍትህን ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል, አልማ ፴፬፥፲፮. ምህረት ፍትህን ይነጥቃል ብለህ ትገምታለህ, አልማ ፵፪፥፳፭ (አልማ ፵፪፥፲፫–፳፭). ህጻናት በክርስቶስ ምህረት ህያው ሆነዋል, ሞሮኒ ፰፥፲፱–፳ (ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮). የኢየሱስ ክርስቶስ ምህረት ክንድ ለሃጢያታችሁ ክፍያ ሆነ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፩. በስሜ የሚያምኑት ሁሉ፣ ባፈሰስኩት ደሜ በአብ ፊት አማልጄላቸዋለሁ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፬. ቃል ኪዳንን የሚያከብሩት ምህረትን ያገኛሉ, ት. እና ቃ. ፶፬፥፮. እኔ ጌታ ኃጥያቶችን ስለምሰርይ፣ እና ኃጥያታቸውን በትሁት ልቦች ለሚናዘዙት በምህረት የተሞላሁ ነኝ, ት. እና ቃ. ፷፩፥፪. እኔ ጌታ ለቅን ሁሉ ምህረት አሳያለሁ, ት. እና ቃ. ፺፯፥፪. እና እንደ ትንሽ ልጅ የሚቀበልህም፣ መንግስቴን ይቀበላል፤ ይማራሉና, ት. እና ቃ. ፺፱፥፫. ምህረት በፊት ለፊትህ ይሄዳል, ሙሴ ፯፥፴፩.