መብት ደግሞም ባርነት; ነጻ ምርጫ; ነጻ፣ ነጻነት ተመልከቱ በነጻነት ለመስራት እና ለማሰብ የሚኖር ችሎታ። በወንጌል መሰረታዊ መርሆች ታዛዥ መሆን ከኃጢያት መንፈሳዊ ባርነት ሰውን ነጻ ያደርጋል (ዮሐ. ፰፥፴፩–፴፮)። ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ, መዝ. ፻፲፱፥፵፭. የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ, ፪ ቆሮ. ፫፥፲፯. ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ, ገላ. ፭፥፩ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፹፮). ሰዎች ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው, ፪ ኔፊ ፪፥፳፯. ይህ ምድር የነፃነት ምድር ይሆናል, ፪ ኔፊ ፲፥፲፩. ሞሮኒ በኔፋውያን መካከል የነፃነት ዓርማው እንዲሰቀል አደረገ, አልማ ፵፮፥፴፮. ጌታ እና አገልጋዮቹ ለታሰሩት ነጻነትን አወጁ, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፲፰፣ ፴፩፣ ፵፪.