ቁጣ ደግሞም መጥላት፣ ጥላቻ; ፍቅር ተመልከቱ ቁጣ የግልፍተኝነት ስሜት የምታይበት ነው። ጌታ ቅዱሳን ቁጣቸውን እንዲቆጣጠሩ አስጠነቀቃቸው (ማቴ. ፭፥፳፪)። ወላጅ ወይም ልጅ ሌሎች ቤተሰብን ማጎሳቆል አይገባቸውም። (፪ ኔፊ ፲፭፥፳፭፤ ት. እና ቃ. ፩፥፲፫) ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ, ዘፍጥ. ፬፥፭. እግዚአብሔር ከቍጣ የራቀ፣ እና ምሕረቱም ብዙ ነው መዝሙረ ዳዊት, መዝ. ፻፵፭፥፰. የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች, ምሳ. ፲፭፥፩. ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል, ምሳ. ፲፭፥፲፰ (ምሳ. ፲፬፥፳፱). ስለ ስሜ ቍጣዬን አዘገያለሁ, ኢሳ. ፵፰፥፱. ዘወትር ወደሚያስቆጡኝ ህዝቦች እጆቼን ዘረጋሁ, ኢሳ. ፷፭፥፪–፫. ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት, ማቴ. ፭፥፴፱. እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው, ኤፌ. ፮፥፬. እውነቱን ስለነገርኳችሁ ተቆጥታችሁኛል, ሞዛያ ፲፫፥፬. ይህንን ህዝብ በቁጣ እጎበኘዋለሁ, አልማ ፰፥፳፱. በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ከማይመሰክሩ በቀር፣ በምንም ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳፩. እኔ ጌታም በኅጥያተኞቹ ተናድጄአለሁ, ት. እና ቃ. ፷፫፥፴፪.