የጥናት እርዳታዎች
ነቢይ


ነቢይ

በእግዚአብሔር የተጠራ እናም እርሱን በመወከል የሚናገር ሰው። እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ፣ ነቢይ ትእዛዛትን፣ ትንቢቶችን፣ እና ራዕዮችን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ይችላል። የእርሱም ሀላፊነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና እውነተኛ ጸባይ ለሰው ዘር ለማሳወቅ እና እርሱ ከእነርሱ ጋር ያለውን ግንኙነት ትርጉም ማሳየት ነው። ነቢይ ኃጢያትን ይወቅሳል እናም የዚህን ውጤቶች አስቀድሞ ይነግራል። እርሱም የጽድቅ ሰባኪ ነው። አንዳንዴም፣ ነቢያት ለሰው ዘር ጥቅም ስለወደፊት አስቀድመው ይናገራሉ። የእርሱ ዋና ሀላፊነት ግን ስለኢየሱስ ክርስቶስ መመስከር ነው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት ዛሬ በምድር ላይ ያለ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው። ቀዳሚ አመራር እና አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት እንደ ነቢያት፣ ባለራዕዮች፣ እና ገላጮች ይደገፋሉ።