ያሬድ ደግሞም የያሬድ ወንድም; ያሬዳውያን ተመልከቱ ከወንድሙ ጋር የህዝብ ቡድንን ከባቢሎን ማማ በምዕራብ ክፍለ አለም ወደሚገኘው የቃል ኪዳን ምድር መርቶ ያወጣ የመፅሐፈ ሞርሞን መሪ (ኤተር ፩፥፴፫–፪፥፩)። ያሬድ ወንድሙን የቤተሰቦቻቸውን እና የወንድሞቻቸውን ቋንቋ ጌታ እንዳያምታታ እንዲጸልይ ጠየቀ, ኤተር ፩፥፴፬–፴፯. ወደ ባሕር ተጓዙ እናም ለአራት ዓመታት በእዚያ ኖሩ, ኤተር ፪፥፲፫. ወደ ቃል ኪዳን ምድር በመርከብ ሄዱ, ኤተር ፮፥፬–፲፪.