መስደብ
ወደ እግዚአብሔር ወይም ወደ ቅዱስ ነገሮች ክብር በማጣት ወይም አክብሮት ባለመኖር መናገር።
ኃጥያቶችን ለማሰረየት መብት ይገባኛል ስላለ (ማቴ. ፱፥፪–፫፤ ሉቃ. ፭፥፳–፳፩)፣ እራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ ብሎ ስለጠራ (ዮሐ. ፲፥፳፪–፴፮፤ ፲፱፥፯)፣ እና እርስን በሀይል ቀኝ ስቀመጥ እና በሰማይ ደመና ስመጣ ታዩኛላችሁ ስላላቸው (ማቴ. ፳፮፥፷፬–፷፭) አይሁዶች ኢየሱስ ስድብ ተናግሯል በማለት በብዙ ጊዜ ከሰውት ነበር። ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ባይሆን ኖሮ እነዚህ ክሶች እውነት ይሆኑ ነበር። በሳንሀድሪን ፊት ለፍርድ በቀረበበት ጊዜ በሀሰት ምስክሮች የተከሰሰበትም (ማቴ. ፳፮፥፶፱–፷፩) የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ተሳድቧል የሚል ነበር ስለክርስቶስ ፍጹም የሆነ እውቀትን ከመቀበል በኋላ በፍልጎት መካድ የሆነው መንፈስ ቅዱስን መስደብ ይቅርታ የሌለው ኃጢያት ነው (ማቴ. ፲፪፥፴፩–፴፪፤ ማር. ፫፥፳፰–፳፱፤ ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፯)።