የነፃነት አርማ ደግሞም ሞሮኒ፣ ሻምበል ተመልከቱ በመፅሀፈ ሞርሞን ውስጥ፣ በኔፋውያን ወታደሮች ዋና መሪ ሞሮኒ የተነሳ አርማ። ሞሮኒ አርማውን የሰራም የኔፋውያን ህዝቦች ሀይማኖታቸውን፣ ነጻነታቸውን፣ ሰላማቸውን፣ እና ቤተሰቦቻቸውን ለመጠበቅ ለማነሳሳት ነበር። ሞሮኒ ኮቱን ቀድዶ የነፃነት አርማ ሰራ, አልማ ፵፮፥፲፪–፲፫. አርማውን የሚደግፉ ቃል ኪዳን ገቡ, አልማ ፵፮፥፳–፳፪. ሞሮኒ በሰገነት ላይ የነፃነት ዓርማው እንዲሰቀል አደረገ, አልማ ፵፮፥፴፮ (አልማ ፶፩፥፳).