ሞአብ ደግሞም ሎጥ ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ጊዜ በሙት ባህር በስተምስራቅ በኩል የሚገኝ ምድር። ሞዓባውያን የሎት ትውልዶች ነበሩ እናም ከእስራኤላውያን ጋር ዘመድ ነበሩ። ከዕብራውያን ቋንቋ ጋር የሚመሳሰል ቋንቋ ነበራቸው። በሞአባውያንና በእስራኤላውያን መካከል የማይቆም ጦርነት ነበረ (መሳ. ፫፥፲፪–፴፤ ፲፩፥፲፯፤ ፪ ሳሙ. ፰፥፪፤ ፪ ነገሥ. ፫፥፮–፳፯፤ ፪ ዜና ፳፥፩–፳፭፤ ኢሳ. ፲፭)።