ይሁዳ፣ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የይሁዳ መልዕክት ጸሀፊ
በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ከኢየሱስ ወንድሞች አንዱ እናም ምናልባት የይሁዳ መልእክት ጸሀፊ (ማቴ. ፲፫፥፶፭፤ ይሁዳ ፩፥፩)።
የይሁዳ መልእክት
ይህ መፅሐፍ በእምነታቸው እየደከሙ ላሉት ቅዱሳን ይሁዳ የጻፈው ደብዳቤ ያለበት ነው። የሚዳከሙትም በመካከላቸው ክርስትያን ነን የሚሉ ግን በስነ ምግባር ጥሩ ያልሆነው ጣዖት አምላኪ እና የስነምግባር ህግን የሚያከብሩ ምሳሌዎች ነን በሚሉት ነበር። ይሁዳ ስለመንፈሳዊ አደጋ ለማስነቃት እና ታማኝ እንዲሆኑ ለማበረታታት ፈልጎ ነበር።
በይሁዳ መልእክት ውስጥ መጠቀስ ከሚገባቸው ውስጥ አንዳንዶቹ ቁጥር ፮ ውስጥ ስለሰማይ ጦርነትና ስለሉስፈርና መላዕክቱ ከቅድመ ምድር ህይወት መጣል የሚናገረው (አብር. ፫፥፳፮–፳፰)፣ እና በቁጥር ፲፬–፲፭ ውስጥ በሔኖክ ትንቢትን መጥቀሱ ነበር።