ነህምያ
በብሉይ ኪዳን ውስጥ በባቢሎን የነበረ በአርጤክስስ ቤተ መንግስት ውስጥ ጠጅ አሳላፊው የነበረ፣ ከእርሱም የኢየሩሳሌም ግንብን እንደገና ለመገንባት ንጉሳዊ ፈቃድ ያገኘ እስራኤላዊ መኰንን (እርሱ ምናልባት ሌዋውያን ወይም የይሁዳ ጎሳ አባል ነበር)።
መፅሐፈ ነህምያ
ይህ መፅሐፍ ከመፅሐፈ ዕዝራ የሚቀጥል ነው። ይህም አይሁዶች ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ በእስራኤል የነበረው ስራ ድርጊቶችን እና ችግሮችን ታሪክ የያዘ ነው። ምዕራፍ ፩–፯ ነህምያ ኢየሩሳሌምን ለመጀመሪያ ጊዜ ስለጎበኘበትና፣ ምንም እንኳን ብዙ ተቃዋሚዎች ቢኖሩም ስለከተማዋ ግንቦች በድጋሚ መገንባት ይናገራሉ። ምዕራፍ ፰–፲ ነህምያ በተግባር ላይ ለማዋል ስለሞከረው የሀይማኖት እና የህብረተሰብ መሻሻል ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፲፩–፲፫ ብቁ የሆኑትን ሰዎች ስም ይሰጣሉ እናም ስለግንቡ መቀደስ ታሪክም ይነግራሉ። በምዕራፍ ፲፫ ቁጥሮች ፬–፴፩ ውስጥ ነህምያ ለአስራ ሁለት አመት ከእዚያ ከሄደ በኋላ፣ ኢየሩሳሌምን ለሁለተኛ ጊዜ ስለጎበኘበት ይመዘግባሉ።