በመጀመሪያው የግሪክ ጽሁፍ “መንከር” ወይም “መጥለቅ” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ተጠቅሞ ነበር። ስልጣን ባለው በውሀ ውስጥ በማጥለቅ መጠመቅ የወንጌሉ ማስተዋወቂያ ስርዓት ነው እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን አባል ለመሆን አስፈላጊ የሆነም ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት እና ንስሀ መግባት ከዚህ በፊት አስቀድመው የሚመጡ ናቸው። እንዲፈጸምም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን መቀበል ይህን መከተል አለበት (፪ ኔፊ ፴፩፥፲፫–፲፬)። ሰው ወደሰለስቲያል መንግስት ከመግባቱ በፊት በውሀ እና በመንፈስ መጠመቁ አስፈላጊ ነው። አዳም በጥምቀት የመጀመሪያው ነው (ሙሴ ፮፥፷፬–፷፭)። ኢየሱስም ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም እና ለሰው ዘር መንገድን ለማሳየት ተጠመቀ (ማቴ. ፫፥፲፫–፲፯፤ ፪ ኔፊ ፴፩፥፭–፲፪)።
በስጋዊ ህይወት ሁሉም በምድር ላይ ያሉት ወንጌልን ለመቀበል እድል ስለማይኖራቸው፣ ጌታ ለሙታን በመኪል ለሚፈጸም ጥምቀት ፈቃድ ሰጥቷል። ስለዚህ፣ በመንፈስ አለም ወንጌልን የሚቀበሉ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ብቁ ለመሆን ይችላሉ።