ሞርሞን (ሞርሞኖች)
ሞርሞን የተባለው ቅፅል ስም የተሰጠው የቤተክርስቲያኗ አባል ያልሆኑት ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትን ለመጠቆም ነበር። ስሙም የመጣው በጥንት ነቢይ ሞርሞን የተዘጋጀና መፅሐፈ ሞርሞን ከተባለው ቅዱሣት መጻህፍት ነው። ጌታ የቤተክርስቲያኗ አባላት እንዲጠሩበት የተሰጣቸው ስም “ቅዱሳን” ነው። የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ ስምም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።