ቤት ደግሞም ቤተሰብ ተምለከቱ ቤት የወንጌል እና የቤተሰብ ስራዎች ዋና ቦታ መሆን ይገባዋል። ሰው የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት, ዘዳግ. ፳፬፥፭. ወደ ቤቱም ሰደደው, ማር. ፰፥፳፮. ልጆች ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘ, ፩ ጢሞ. ፭፥፬. ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ ሁኑ, ቲቶ ፪፥፭. ወደ ቤታችሁ ሂዱ፣ እናም ስለተናገርኳችሁ ነገሮች አሰላስሉ, ፫ ኔፊ ፲፯፥፪–፫. በድፍረት እንዲቆሙ፣ እናም ለሚስቶቻቸው፣ እናም ለልጆቻቸው፣ ለመኖሪያቸው እናም ለቤታቸው እንዲዋጉ በታላቅ ሀይል ተናገርኩአቸው, ሞር. ፪፥፳፫. አባቶች በቤትም ቅን እና አሳቢ እንዲሆኑ ታዝዘዋል, ት. እና ቃ. ፺፫፥፵፫–፵፬፣ ፵፰–፶.