ፍርድ፣ የመጨረሻው ደግሞም መኮነን፣ ኩነኔ; ኢየሱስ ክርስቶስ—ዳኛ; ዳኛ፣ ፍርድ ተመልከቱ ከትንሳኤ በኋላ የሚመጣ የመጨረሻው ፍርድ። እግዚአብሔር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፣ እያንዳንዱን ሰው የትኛው ዘለአለማዊ ክብር ለማግኘት እንደሚገባው የሚወስንበት ፍርድ። ይህ ፍርድ የሚመሰረተው የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት ከመቀበል በተጨማሪ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በሚያከብርበት ነው። አብ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቷል, ዮሐ. ፭፥፳፪. ሁላችንም በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን, ሮሜ ፲፬፥፲. ሙታን በመጻሕፍት ተጽፎ በነበረው ይፈረድባቸዋል, ራዕ. ፳፥፲፪ (ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፮–፯). ለሥራህ ሁሉ ወደ ፍርድ ትቀርባለህ, ፩ ኔፊ ፲፥፳. አስራ ሁለት ሐዋርያት እና የኔፋውያን አስራ ሁለት ሐዋሪያት በእስራኤል ላይ ይፈርዳሉ, ፩ ኔፊ ፲፪፥፱–፲ (ት. እና ቃ. ፳፱፥፲፪). ሁሉም ሰዎች በእስራኤል ቅዱስ የፍርድ ወንበር ፊት መምጣት አለባቸው, ፪ ኔፊ ፱፥፲፭. ለዚያ ለታላቁ ቀን ራሳችሁን አዘጋጁ, ፪ ኔፊ ፱፥፵፮. በእግዚአብሔር ፍርድ ቤት ፊት መቅረባችሁን መገመት ይቻላችኋልን, አልማ ፭፥፲፯–፳፭. ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለመፍረድ ይቆማል, ፫ ኔፊ ፳፯፥፲፮. ጌታ ኀጢያተኞች ላይ ሁሉ ለፍርድ እርግማን ይዞ በምድር ላይ ይወርዳል, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፪.