መጠነኛነት ደግሞም ትሁት፣ ትሕትና ተመልከቱ ትሁት፣ መጠነኛ፣ እና ጨዋ የሆነ ጸባይ እና አመለካከት። መጠነኛ የሆነ ሰው ከመጠን በላይ የሆኑትን እና ሽንገላን ያስወግዳል። እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሔዋን የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው, ዘፍጥ. ፫፥፳፩ (ሙሴ ፬፥፳፯). ሴቶች በሚገባ ልብስ ሰውነታቸውን ይሸልሙ, ፩ ጢሞ. ፪፥፱. ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ ሁኑ, ቲቶ ፪፥፭. ብዙዎች በልብሳቸው ውድነት አንገታቸውን አደንድነዋል, ያዕቆ. ፪፥፲፫. ልብሶችህ ያላጌጠ ይሁኑ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፵. በንፁህነት፣ በምግባረ ጥሩነት፣ በመሆን እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፫.