ኔሆር ደግሞም የካህን ተንኮል; የክርስቶስ ተቃዋሚ ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የነበረ ክፉ ሰው። ኔሆር በኔፋውያን መካከል የካህናት ተንኮል ከሰሩት የመጀመሪያው ነበር። የሀሰት ትምህርትን ካስተማረና ጌዴዎንን ከገደለ በኋላ፣ ኔሆር ለወንጀሉ በሞት ተቀጣ (አልማ ፩)። የኔሆር ተከታዮች ኔሆር ከሞተ ከረጅም ጊዜ በኋላ የክፉ ስራውንና ትምህርቱን ቀጠሉ። አልማና አሙሌቅ በኔሆር ተከታይ ዳኛ ወደ እስር ቤት ተሰድደው ነበር, አልማ ፲፬፥፲፬–፲፰. የተገደሉት የኔሆርን ኃይማኖት ተከታዮች ነበሩ, አልማ ፲፮፥፲፩. ብዙ የኔሆርን ስርዓት የሚከተሉ ነበሩ, አልማ ፳፩፥፬. ብዙዎቹን ወንድሞቻቸውን የገደሉት የኔሆር ስርዓት የሚከተሉ ነበሩ, አልማ ፳፬፥፳፰.