የጥናት እርዳታዎች
መጸጸት፣ ንስሀ መግባት


መጸጸት፣ ንስሀ መግባት

ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ እራስ፣ እና በአጠቃላይም ወደ ህይወት አዲስ አስተሳሰብ የሚያመጣ የአዕምሮና የልብ ቅያሬ። ንስሀ መግባት ሰው ከክፋት መዞሩን እና ልቡንና ፍላጎቱን ወደ እግዚአብሔር ማዞሩን፣ በእግዚአብሔር ትእዛዛትና ፍላጎት እራስን እንዳስገዛ እና ኃጢያትን እንደተወ ያስመለክታል። እውነተኛ ንስሀ መግባት የሚመጣው ለእግዚአብሔር ባለው ፍቅር እና የእርሱን ትእዛዛት ለማክበር ባለው ልባዊ ፍላጎት ነው። ተጠያቂነት ያላቸው ሰዎች ሁሉ ኃጢያት ሰርተዋል እናም ወደ ደህንነት ወደፊት ለመጓዝ ንስሀ መግባት አለባቸው። ንስሀችን ውጤታማና በእግዚአብሔር ተቀባይነት የሚያገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ብቻ ነው።