አልማ፣ የአልማ ወንድ ልጅ
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የኔፋውያን ህዝቦች የመጀመሪያ ዋና ዳኛ እና ነቢይ። በወጣትነቱ ቤተክርስትያኗን ለማጥፋት ፈለገ (ሞዛያ ፳፯፥፰–፲)። ነገር ግን፣ መላእክት ተገለጸለት እና ወደ ወንጌሉም ተቀየረ (ሞዛያ ፳፯፥፰–፳፬፤ አልማ ፴፮፥፮–፳፯)። በኋላም የዋና ዳኛ ሀላፊነቱን ህዝቦችን ለማስተማር ዘንድ ተወው (አልማ ፬፥፲፩–፳)።
መፅሐፈ አልማ
የነብያት አልማ፣ የአልማ ልጅ፣ እና የእርሱም ልጅ ሔለማን ፅሁፎች በእጥረት ተፅፎበት ያለ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የተለየ መፅሐፍ። በመፅሐፉ ውስጥ የሚገለጹት ድርጊቶች የደረሱት በግምት ከ ፺፩ እስከ ፶፪ ም.ዓ. ነበር። መፅሀፉ ፷፫ ምዕራፎች አሉት። ምዕራፍ ፩–፬ የኔሆር እና የአምሊካይ ተከታዮች በኔፋውያን ላይ ያመጹበትን ይገልጻሉ። የዚህ ውጤት ጦርነት በኔፋውያን ታሪክ ውስጥ ከነበሩት በላይ የሚያጠፋ ነበር። ምዕራፍ ፭–፲፮ የአልማን የመጀመሪያ የሚስዮን ጉዞዎች፣ በተጨማሪም የጥሩው እረኛ ስብከቱን (አልማ ፭) እና ከአሙሌቅ ጋር በአሞኒያሀ ውስጥ የሰበከውን ፅሁፍ ይዘዋል። ምዕራፍ ፲፯–፳፯ የሞዛያ ወንድ ልጆችን እና በላማናውያን መካከል ስላደረጉት አገልግሎት ፅሑፍ ይዘዋል። ምዕራፍ ፳፰–፵፬ የአልማ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የነበሩትን አንዳንድ ስብከቶች ይዘዋል። በምዕራፍ ፴፪ ውስጥ አልማ ቃልን ከዘር ጋር አነጻጸረ፤ በምዕራፍ ፴፮ ውስጥ ለልጁ ሔለማን የቅያሬ ታሪኩን ነገረው። ምዕራፍ ፴፱–፵፪ አልማ በስነምግባር መተላለፍ ተካፋይ ለነበረው ለልጁ ቆሪያንተን የሰጠውን ምክር ይመዘግባሉ፤ ይህ አስፈላጊ ስብከት ፍትህን፣ ምህረትን፣ ትንሳኤን፣ እና የኃጢያት ክፍያን ይገልጻል። ምዕራፍ ፵፭–፷፫ የዛ ጊዜ የኔፋውያን ጦርነቶችን እና በሀጋዝ ዘመን ስደቶችን ይገልጻሉ። እንደ ሻምበል ሞሮኒ፣ ቴአንከም፣ እና ሊሀይ አይነት ታላቅ መሪዎች በብርቱ እና ጊዜአዊ ስራዎቻቸው ኔፋውያንን ለመጠበቅ ረዱ።