ሞሮኒ፣ ሻምበል ደግሞም የነፃነት አርማ ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ በ፻ ም.ዓ. አካባቢ የኖረ ጻድቅ የኔፋውያን የወታደሮች አዛዥ። ሞሮኒ በኔፋውያን ወታደሮች ላይ ሙሉ በሙሉ አዛዥ ነበር, አልማ ፵፫፥፲፮–፲፯. የተነሳሱ የኔፋውያን ወታደሮች ለነጻነታቸው ተዋጉ, አልማ ፵፫፥፵፰–፶. በኮቱ ቁራጩ ላይ የነፃነት አርማ ሰራ, አልማ ፵፮፥፲፪–፲፫. የእግዚአብሔር ሰው ነበር, አልማ ፵፰፥፲፩–፲፰. የሀገራቸውን ነፃነት በተመለከተ በመንግስቱ ግዴለሽነት ተቆጥቶ ነበር, አልማ ፶፱፥፲፫.