የጥናት እርዳታዎች
ኤተር


ኤተር

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የመጨረሻው የያሬዳውያን ነቢይ (ኤተር ፲፪፥፩–፪)።

መፅሐፈ ኤተር

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የያሬዳውያን ታሪክ መዝገብን የያዘ መፅሐፍ። ያሬዳውያን ከሌሂ ህዝቦች ከብዙ መቶ አመቶች በፊት በምዕራብ ክፍለ አለም ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች። መፅሐፈ ኤተር በሊምሒ ህዝቦች ከተገኙት ሀያ አራት ሰሌዳዎች የተወሰዱ ነበሩ (ሞዛያ ፰፥፰–፱)።

ምዕራፍ ፩–፪ ያሬዳውያን በባቢሎን ግንብ መገንባት ጊዜ ቤታቸውን ትተው አሁን የአሜሪካ ክፍለ አህጉር ተብሎ ወደሚታወቀው እንዴት እንደሄዱ ይናገራሉ። ምዕራፍ ፫–፮ የያሬድ ወንድም የቅድመ ምድራዊ አዳኝን እንዳየና ያሬዳውያን በስምንት ጀልባዎች እንደተጓዙ ይገልጻል። ምዕራፍ ፯–፲፩ የያሬዳውያን ታሪክ ውስጥ በብዛት የሚገኘውን የክፋትነት ታሪክን ቀጠሉ። የኤተር መዝገብን ያዘጋጀው ሞሮኒ ምዕራፍን ፲፪–፲፫ን በእምነት ስለተደረጉ ታምራቶች እና ስለ ክርስቶስ እና ስለምትመጣው አዲስቷ ኢየሩሳሌም ጻፈ። ምዕራፍ ፲፬–፲፭ ያሬዳውያን እንዴት ታላቅ ሀገሮች እንደሆኑ ነገር ግን በኃጢያተኝነት ምክንያት በመጣ ህዝባዊ ጦርነት እንደተደመሰሱ ይናገራል።