ቅንዓት፣ መቅናት ደግሞም ቅናት ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደተጻፉት፣ ቅንዓት ማለት፥ (፩) የጋለ መሆን እና ስለአንድ ሰው ወይም ነገር ጥልቅ ስሜት መኖር፣ እና (፪) በሰው መቅናት ወይም ሌላ በእናንተ ላይ እድል ይኖረዋል በማለት መጠራጠር። የጋለ ስሜት መኖር እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ, ዘፀአ. ፳፥፭ (ዘዳግ. ፭፥፱; ፮፥፲፭; ሞዛያ ፲፩፥፳፪). ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ, ሕዝ. ፴፱፥፳፭. በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ, ዘካ. ፩፥፲፬. መቅናት ወይም መጠራጠር ቅንዓት ለሰው የቍጣ ትኵሳት ነው, ምሳ. ፮፥፴፪–፴፭. አኪሽም በወንድ ልጁ መቅናት ጀመረ, ኤተር ፱፥፯. ከቅናት እና ፍርሀት ራሳችሁን አስወግዱ, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲.