ቤዛ፣ ማዳን፣ ቤዛነት ደግሞም መንፈሳዊ ሞት; ስጋዊ ሞት; ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; የአዳም እና የሔዋን ውድቀት; ደህንነት ተመልከቱ ሰውን ከባሪያነት ለማዳን እንደመክፈል አይነት፣ ማዳን፣ መግዛት፣ ወይም ለማዳን መክፈል። ቤዛነት የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያን እና ሰው ከኃጢያት መዳንን ይጠቅሳል። የኢየሱስ የኃጢያት ክፍያ የሰውን ዘር ከስጋዊ ሞት ያድናል። በኃጢያት ክፍያም፣ በእርሱ እምነት ያላቸው እና ንስሀ የሚገቡት ከመንፈስ ሞትም ድነዋል። ተቤዥቼሃለሁ, ኢሳ. ፵፬፥፳፪. ከሞትም እቤዣቸዋለሁ, ሆሴ. ፲፫፥፲፬ (መዝ. ፵፱፥፲፭). በክርስቶስ ደም የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን, ኤፌ. ፩፥፯፣ ፲፬ (ዕብ. ፱፥፲፩–፲፭; ፩ ጴጥ. ፩፥፲፰–፲፱; አልማ ፭፥፳፩; ሔለ. ፭፥፱–፲፪). ጌታ ነፍሴን ከሲኦል አድኗታል, ፪ ኔፊ ፩፥፲፭. ቤዛነት የሚመጣው በቅዱስ መሲሕ በኩል ይመጣል, ፪ ኔፊ ፪፥፮–፯፣ ፳፮ (ሞዛያ ፲፭፥፳፮–፳፯; ፳፮፥፳፮). በቤዛነት ፍቅር ዘምረዋል, አልማ ፭፥፱ (አልማ ፭፥፳፮; ፳፮፥፲፫). ለኃጢአተኞች የሞት እስር ከመፈታት በስተቀር ቤዛነት እንዳልተፈፀመ ሆነው ይቆያሉ, አልማ ፲፩፥፵–፵፩ (አልማ ፴፬፥፲፮; ፵፪፥፲፫; ሔለ. ፲፬፥፲፮–፲፰). ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነትን አምጥቷል, ሞር. ፯፥፭–፯. የቤዛነት ኃይል ህጉ ለሌላቸው ሁሉ ይመጣል, ሞሮኒ ፰፥፳፪ (ት. እና ቃ. ፵፭፥፶፬). የማያምኑት ከመንፈሳዊ ውድቀታቸው አይድኑም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፬. ህፃናት ከአለም መጀመሪያ ጀምሮ በአንድያ ልጄ ድነዋል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮. ሕዝቡን ጌታ አድኗል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፺፱. ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ በራዕይ የሙታን ቤዛነትን አዩ, ት. እና ቃ. ፻፴፰. አዳም እና ሔዋን በቤዛነታቸው ተደሰቱ, ሙሴ ፭፥፱–፲፩.