ኢያሪኮ በዮርዳኖስ ሸለቆ ውስጥ ከባህር በ፪፻፵፭ ሜትር ዝቅ ያለች በግንብ የተከበበች ከተማ። ኢያሪኮ እስራኤላውያን ወደ ቃል ኪዳን ምድር ለመጀመሪያ በገቡበት ጊዜ ወንዙን የተሻገሩበት ቦታ አጠገብ ነው (ኢያ. ፪፥፩–፫፤ ፫፥፲፮፤ ፮)። እስራኤላውያን በኢያሪኮ በጦርነት ተዋጉ, ኢያ. ፮፥፩–፳. ኢያሱ ኢያሪኮን ረገመ, ኢያ. ፮፥፳፮ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፴፬). ኢያሪኮ ለቢንያም በተመደበው ግዛት ውስጥ ነበር, ኢያ. ፲፰፥፲፩–፲፪፣ ፳፩. ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ በሚጓዝበት ጊዜ ኢያሪኮን ጎበኘ, ማር. ፲፥፵፮ (ሉቃ. ፲፰፥፴፭; ፲፱፥፩).