ጸሎት
ከእግዚአብሔር ጋር በአምልኮ በመነጋገር ሰው ምስጋናዎች የሚሰጥበት እና በረከቶችን የሚጠይቅበት መንገድ። ጸሎት የሚቀረቡት ለሰማይ አባት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው። ጸሎቶች በከፍተኛ ድምፅ ወይም በጸጥታ ለመቅረብ ይችላሉ። የሰው ሀሳቦች ወደ እግዚአብሔር የሚመሩ ከሆኑ ጸሎት ለመሆን ይችላሉ። የጻድቅ መዝሙር ለእግዚአብሔር ጸሎት ይሆናል (ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፪)።
የጸሎት አላማ የእግዚአብሔርን ፍላጎት ለመቀየር ሳይሆን፣ ለእራሳችን እና ለሌሎች እግዚአብሔር ፍላጎቱን ለመስጠት የሚፈለገውን በረከቶችን ለማግኘት ነው፣ ነገር ግን ያን ለማግኘት መጠየቅ አለብን።
ለአብ በክርስቶስ ስም እንጸልያለን (ዮሐ. ፲፬፥፲፫–፲፬፤ ፲፮፥፳፫–፳፬)። ምኞታችን የክርስቶስ ምኞት ሲሆኑ በእውነትም በክርስቶስ ስም ለመጸለይ እንችላለን (ዮሐ. ፲፭፥፯፤ ት. እና ቃ. ፵፮፥፴)። ከእዚያም እግዚአብሔር ሊሰጣቸው የሚችለውን ትክክለኛ ነገሮችን ለመቀበል እንጠይቃለን (፫ ኔፊ ፲፰፥፳)። አንዳንድ ጸሎቶች መልስ አያገኙም ምክንያቱም እነዚህ የክርስቶስ ፍላጎት ስላልሆኑ ግን ከሰው የራስ ወዳድነት የሚመጡ ስለሆኑ ነው (ያዕ. ፬፥፫፤ ት. እና ቃ. ፵፮፥፱)። በእርግጥም፣ ጻድቅ ላልሆኑ ነገሮች እግዚአብሔርን ከጠየቅን፣ ይህም ያስኮንነናል፣ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፭)።