ሰውነት ደግሞም ስጋዊ ሞት; ስጋዊ፣ የሚሞት; ትንሳኤ; ነፍስ ተመልከቱ በእግዚአብሔርም ምስል ተፈጥሮ ከመንፈስ ጋር በመጣመር ህያው ሰውን የሚሰራ ስጋዊ፣ የስጋና የአጥንት የሰውነት አካል። የወንድ እና ሴት ሰዎች አካላዊ ሰውነቶች በትንሳኤ ከመንፈሳቸው ጋር ለዘለአለም ተመልሰው ይጣመራሉ። ቅዱሣት መጻህፍት አብረው የተጣመሩትን ሰውነት እና መንፈስ እንደ ነፍስ ይጠሩታል (ዘፍጥ. ፪፥፯፤ ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፭፤ ሙሴ ፫፥፯፣ ፱፣ ፲፱፤ አብር. ፭፥፯)። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው, ዘፍጥ. ፪፥፯ (ሙሴ ፫፥፯). መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ, ሉቃ. ፳፬፥፴፱. ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ, ፩ ቆሮ. ፱፥፳፯. ፍጥረታዊ አካል አለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፵፬. ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ ነው, ያዕ. ፪፥፳፮. የሚሞተው ሰውነት ወደ ማይሞተው ሰውነት ይነሳል, አልማ ፲፩፥፵፫–፵፭. ማንኛውም የሰውነት ክፍል ወደ ቀድሞው ይመለሳል, አልማ ፵፩፥፪. ኢየሱስ ከሞት የተነሳውን ሰውነቱን ለኔፋውያን አሳየ, ፫ ኔፊ ፲፥፲፰–፲፱፤ ፲፩፥፲፫–፲፭. አብ እንደ ሰው ተጨባጭ የሆነ የስጋ እና አጥንቶች ሰውነት አለው፣ ወልድም ደግሞ እንዲሁ አለው, ት. እና ቃ. ፻፴፥፳፪. እግዚአብሔር በእርሱ ሰውነት አምሳል ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው, ሙሴ ፮፥፱ (ዘፍጥ. ፱፥፮).