የሞት ቅጣት ደግሞም ግድያ ተመልከቱ ለተሰራ ወንጀል፣ በልዩም ከግድያ ቅጣት ጋር የተያያዘ፣ የሞት ቅጣት። የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ በሰው ይፈስሳል, ዘፍጥ. ፱፥፮ (ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፱፥፲፪–፲፫). ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል, ዘኁል. ፴፭፥፲፮. እያወቀ የሚገድል ይሞታልና, ፪ ኔፊ ፱፥፴፭. በህግ መሰረት እንድትሞት ተፈርዶብሀል, አልማ ፩፥፲፫–፲፬. የገደለውም በሞት ተቀጥቷል, አልማ ፩፥፲፰. ህጉ የገደለውን ሰው ህይወት ይጠይቃል, አልማ ፴፬፥፲፪. የሚገድልም ይገደላል, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፱.