ዔሳው ደግሞም ያዕቆብ፣ የይስሐቅ ልጅ; ይስሐቅ ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የይስሀቅ እና የርብቃ የመጀመሪያ ልጅ እና የያዕቆብ መንታ ወንድም። ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ ወንድሞች ይፎካከሩ ነበር (ዘፍጥ. ፳፭፥፲፱–፳፮)። የዔሳው ትውልዶች፣ ኤዶማውያን፣ እና የያዕቆብ ትውልዶች፣ እስራኤላውያን፣ የሚፎካከሩ ሀገሮች ሆኑ (ዘፍጥ. ፳፭፥፳፫)። ዔሳው ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ, ዘፍጥ. ፳፭፥፴፫ (ዕብ. ፲፪፥፲፮–፲፯). ዔሳው ወላጆቹን በማሳዘን የኬጢ ሚስቶች አገባ, ዘፍጥ. ፳፮፥፴፬–፴፭. ያዕቆብ እና ዔሳው ታረቁ, ዘፍጥ. ፴፫.