ግብረ ሰዶማዊ ጸባይ ደግሞም ማመንዘር; ስሜታዊ፣ ስሜታዊነት ተመልከቱ አንድ አይነት ጾታ ያላቸው ሰዎች የግብረ ገብ ግንኙነት። እግዚአብሔር እንደዚህ አይነት የግብረ ስጋ ግንኙነትን ከልክሏል። እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው, ዘፍጥ. ፲፱፥፩–፲፩ (ሙሴ ፭፥፶፩–፶፫). ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነው, ዘሌዋ. ፲፰፥፳፪ (ዘሌዋ. ፳፥፲፫). ከእስራኤልም ወንዶች ልጆች ወንድ ጋለሞታ አይገኝ, ዘዳግ. ፳፫፥፲፯. እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፥ አይሠውሩአትም, ኢሳ. ፫፥፱ (፪ ኔፊ ፲፫፥፱). ወንዶች እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ, ሮሜ ፩፥፳፯. ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም, ፩ ቆሮ. ፮፥፱–፲. ከወንድ ጋርም ለሚተኙ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ ለጻድቅ አልተሰራም, ፩ ጢሞ. ፩፥፱–፲. ሌላን ሥጋ የተከተሉ፣ በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል, ይሁዳ ፩፥፯.