ዕጣ የተለያዩ ምርጫዎችን የሚመረጥበት ወይም የሚወገድበት መንገድ፣ በብዙም ጊዜ የሚደረገው አንድ ወረቀትን ወይም እንጨትን ለብዙዎች መካከል በመምረጥ ነው። ይህም እጣ መጣል ይባላል። ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ, ማቴ. ፳፯፥፴፭ (መዝ. ፳፪፥፲፰; ማር. ፲፭፥፳፬; ሉቃ. ፳፫፥፴፬; ዮሐ. ፲፱፥፳፬). ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀ, የሐዋ. ፩፥፳፫–፳፮. ማን ወደ ላባን ቤት መሄድ እንዳለበት ዕጣ ተጣጣልን, ፩ ኔፊ ፫፥፲፩.