ከፍተኛነት ደግሞም ሰው፣ ሰዎች—የሰው እንደ እግዚአብሔር አይነት ለመሆን ያለው ችሎታ; አክሊል; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; የሰለስቲያል ክብር; የዘለዓለም ህይወት ተመልከቱ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ታላቁ የደስታና የክብር ሁኔታ ከፊትህ ጋር ደስታ, መዝ. ፲፮፥፲፩. እነርሱ አማልክቶች፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው—ስለዚህ፣ ሁሉም ነገሮች የእነርሱ ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶፰–፶፱. ቅዱሳንም ውርሳቸውን ይቀበላሉ እና ከእርሱም ጋር እኩል ይደረጋሉ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፯. እነዚህ መላእክቶች በህጎቼ አልኖሩም፤ ስለዚህ፣ ተለያይተው እና በብቸኝነት፣ ያለዘለአለማዊነት ይቆያሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፲፯. ወንዶች እና ሴቶች ዘለአለማዊነትን ለማግኘት በእግዚአብሔር ህግ መሰረት መጋባት አለባቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፲፱–፳. ወደ ዘለአለማዊነት መቀጠል የሚወስደው ደጅ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፪–፳፫. አብርሐም ይስሀቅ፣ እና ያዕቆብ ወደ ዘለአለማዊነታቸው ገብተዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፱፣ ፴፯. ዘለአለማዊነትህን አትምብሀለሁ, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፵፱.