የማይሞት፣ አለሟችነት ደግሞም ስጋዊ፣ የሚሞት; ትንሳኤ; ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ደህንነት ተመልከቱ ለዘለአለም ከሞት በተነሳ ሁኔታ፣ ለስጋዊ ሞት ተገዢ በማይሆንበት የመኖር ጉዳይ። ተነሥቶአል, ማር. ፲፮፥፮. እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉ, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፳፪. የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፣ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፶፫–፶፬. ክርስቶስ ሞትን ሽሮአልና አለመጥፋትን አውጥቶአል, ፪ ጢሞ. ፩፥፲. አለሟችነት ስጋና መንፈስ እንደነበሩ በድጋሚ ማገጣጠም ነው, ፪ ኔፊ ፱፥፲፫. መንፈሶች ከሰውነታቸው ጋር አንድ በመሆን የማይጠፉ የማይሞቱ ይሆናሉ, አልማ ፲፩፥፵፭. ታማኝ በዘላለም ሕይወት ዘውድ አክሊልም ይጫንላችኋል, ት. እና ቃ. ፸፭፥፭. ምድር የተቀደሰች፣ የማትጠፋ ትሆናለች, ት. እና ቃ. ፸፯፥፩ (ት. እና ቃ. ፻፴፥፱). የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት አምጥቶም የማሳለፍ የእግዚአብሔር ስራ እና ክብር ይህ ነው, ሙሴ ፩፥፴፱.