የጥናት እርዳታዎች
መግረዝ


መግረዝ

በብሉይ ኪዳን ዘመናት ለእስራኤል ወንዶች የነበረ የአብርሐም ቃል ኪዳን ምልክት (ዘፍጥ. ፲፯፥፲–፲፩፣ ፳፫–፳፯ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፲፯፥፲፩ [ተጨማሪ])። ግርዘት የወንድ ህጻናትን እና ጎልማሳዎችን “የቍልፈተ ሥጋ” በመቁረጥ የሚፈጸም ነበር። ይህን የሚያደርጉት የቃል ኪዳን መብት ነበራቸው እናም የዚህን ሀላፊነት ይቀበላሉ። ግርዘት በክርስቶስ ተልዕኮ እንደ ቃል ኪዳን ምልክት የተወገደ ነበር (ሞሮኒ ፰፥፰ት. እና ቃ. ፸፬፥፫–፯)።