ጴንጤናዊው ጲላጦስ በይሁዳ ውስጥ ከሮሜ የመጣ ገዢ፤ ከ፳፮–፴፮ ም.ዓ. (ሉቃ. ፫፥፩)። የአይሁዳ ህዝብን እና ሀይማኖታቸውን ይጠላ ነበር እናም አንዳንድ የገሊላ ሰዎችን አስገድሏል (ሉቃ. ፲፫፥፩)። ኢየሱስ ተከሰሰ እናም በጲላጦስ ፊት እንዲሰቀል ተኮነነ (ማቴ. ፳፯፥፪፣ ፲፩–፳፮፣ ፶፰–፷፮፤ ማር. ፲፭፤ ሉቃ. ፳፫፤ ዮሐ. ፲፰፥፳፰–፲፱፥፴፰)።